Skip to main content
የአፍሪቃ_መሪዎች_በዜጎች መካከል አንድነትን ከመፍጠር ይልቅ የብሄር_ፖለቲካን ፖሊሲ በመምረጥ በስልጣን ላይ ለረጅም ጊዜ ለመቆየት እየሰሩ ነው! አምሳሉ_ካሳው EACC
#####
ዴንቨር_ዩንቨርስቲ አዘጋጅነት በተዘጋጀው የአፍሪካ እና  የዲያስፖራ ተሳትፎ እና ሚና ውይይት ላይ የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ተወካይ አቶ አምሳሉ_ፀጋዪ ካሳው የአፍሪቃ ሀገራት ችግሮች መሰረታዊው የብሄር ተኮር ፖለቲካን መምረጣቸው መሆኑን የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በማንሳት የአፍሪቃ ሀገራት ሊሰሩበት የሚገባ ችግር ነው ሲሉ ጥሪ ለተደረገላቸው የአፍሪካ ህብረት አምባሳደሮች እንዲሁም የዩንቨርስቲው የአለም አቀፍ ግንኙነት ተማሪዎች አሳስበዋል።
በአሁኑ ሰኣት አፍሪካ የጦርነት አባዜን ለማጥፋት ደፋ ቀና የሚልበት ሰኣት መሆን አለበት። አዲሱ ኢትዮጵያ መንግስት አንድነትን ያመጣል ለአፍሪካም ተምሳሌት ይሆናል የሚል ጥሩ ጅማሬ የነበረ ቢሆንም የአፍሪቃ መጥፎ ባህል ጫና አድሮጎበት ተመልሶ ወደ ብሄር ፖለቲካ መግባቱ ለአፍሪቃ ጥሩ ተምሳሌት ይሆናል ተብሎ የነበረውን ተስፋ በዲያስፖራው ዘንድ አጨልሟል።
ይህም የሆነው ከራስ አልፎ ለሌላው ያለማሰብን ለእኔ ብች እንጂ ለዜጎች የማይቆረቆርን ብሄራዊ ስሜት ማጣት እና ሙስና እንዲሁም የስልጣን ምቾት አጀማመሮችን መቀየራቸውን አቶ አምሳሉ በፓናል ውይይቱ ላይ ተናግረዋል። አፍሪቃ እንደቀደምትነቷ ወደ ምእራቡ አለም መራመድ ያልቻለቸው ደካማ መሪዎች ብሄራዊነት ስሜት የሚጠፋው ለረጅም ጊዜ ለመቆየት በማሰብ የዘር ፖለቲካን ብቸኛ መንገድ ያደርጉታል ይህ ደግሞ ሁሌም በመገዳደል መተካካትን እየፈጠረ እንዲቀጥል አድርጓታል።
ይህን በዘር የመተካካት በሽታ ለማጥፋት የአፍሪቃ ህብረት እና ዲያስፖራዎች አንድነትና ፍቅርን በዜጎች መካከል በተደጋጋሚ በማስተማር እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከተሰራ የዘር ፖለቲካን የሚያራምዱ እንደ ኢትዮጵያ መንግስት ያሉ ሀገራት በህዝብ ተቀባይነትን ሊያጡ ይችላሉ እና ዲያስፖራው ከፍተኛ የመቻቻል እና አብሮ የመኖር የቀደመ ባህልን የማስተማር ሚና አለበት ሰላምና ፍቅርን ለማምጣት ብለዋል።
የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ይህንን ግምት ውስጥ በከተተ የዘር ብሄር ፖለቲካ በህግ እንዲታገድ ዘመቻ በማድረግ ላይ ቢገኝም የገዥው መንግስት ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆኑ የሚያሳይበት መንገድ በየጊዜው በሀገር ውስጥ የሚከሰቱት ማንነትን መሰረት ያደረጉ ግድያዎች፣ የሃይማኖት ጣልቃ ገብነትና መፈናቅሎች ምሳሌ ናቸው፣ በተመሳሳይ በሱዳንም እንደዚሁ ችግሮች መኖራቸውን አስታውሰው ካውንስሉ የዲያስፖራ ደጋፊዎቹን አስተባብሮ የዲፕሎማሲ ጫናዎችን እየሰራ ነው ብለዋልም ወቀሰዋል።
በፓናል ውይይቱ የተለያዩ ሀገራት ፅሁፍ አቅራቢዎች የነበሩ ሲሆን አምባሳደር ፍሬዲ የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ፣ የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር፣ የደቡብ አፍሪካ፣ ኬኒያ፣ ግብፅ፣ ዛምቢያ፣ ሩዋንዳ፣ ማሊ፣ ኡጋንዳ፣ እና ጥቁር አሜሪካውያን በየተራ ፅሁፍ አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል የሙሉ ቀን ውይይቱ ተጠናቋል።

Leave a Reply